አዲስ ዘመን ነሐሴ 12/2018
Sep 02, 2026
78
Addis Ababa
100 ETB
10%
የተሽከርካሪ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አ/ የም/አም/ኃ/የተ/የግ/ማህበር/0005/2026
አልቪማ የምግብ አምራች ኃ/የተ/የግ/ማህበር የ2020 ሞዴል ያገለገለ ጣልያን አይቪኮ(Model 50C15/53 Year 2020 Chassis no.: EBPBCAHAALD000016: Motor no.:FICE3481138273261 Clour: White Vehicle type: Bus CC: 2998 በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሠረት በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማንኛውም ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይቀናት መጫረት ይችላሉ፡፡
1. ማንኛውም የመጫረት ፍላጎት ያለው, በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላል፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ሲያቀርቡ ለተጫረቱበት ተሽከርካሪ የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10 % (አስር በመቶ) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ከሲፒኦ ዉጪ የሚያቀርቡ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
3. የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች ተሸከርካሪው አዳማ በሚገኘው የድርጅቱ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ በአካል በመቅረብ ማየት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ አሸናፊው ተለይቶ ከታወቀ በኃላ የሚመለስ ይሆናል፡፡
5. የጨረታው አሸናፊ ለተሸከርካሪው የሚከፈሉ ማንኛውንም የመንግስት ከፍያዎችን ሁሉ ይሸፍናል፡፡
6. ማንኛውም ተጫራትች ሌሎች በሰጡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
7. የጨረታው አሸናፊ መሆኑ የተገለፀለት ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው 10% (አስርበመቶ) እንደውል ማስከበሪያ ይቆጠራል፡፡ የጨረታው አሸናፊ የገባውን ውል ካልፈፀም
ለጨረታ መስከበሪያ የተያዘው ዋስትና እንደ ውል ማስከበሪያ ተቆጥሮ የተያዘዉን ገንዘብ አልቪማ የምግብ አምራች ኃ/የተ/የግ/ማህበር ወደ ራሱ ካዝና ገቢ ያደርጋል፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከድርጅቱ ፋይናንስ መምርያ አዳማ ወይንም አዲስ አበባ ከሚገኘው ቢሮ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመከፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
9. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለ 15 (አስራ አምስት) ተከታታይቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ 16ኛው የስራ ቀን ከቀኑ በ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን አዳማ ከተማ በሚገኘው የድርጅቱ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ ከቀኑ በ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ለጨረታ ሰነድ ማስገቢያ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ በጨረታ ሰነዱ ላይ ያልተሞላ ወይንም በሌላ ወረቀት ላይ የተሞላ ዋጋ ተቀባይነት የለውም።
11. የጨረታው አሸናፊ የሚለየው ባቀረበው የመግዣ ዋጋ መሠረት ብቻ ነው።
12. የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ማሸነፉ በተገለጸ በ7 ቀናት ዉስጥ በአካል ቀርቦ ውል መፈፀም አለበት፡፡
13. የጨረታው አሸናፊ ውል እንዲፈፅም በተገለፀለት በ 7 ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል ባይፈፅም ድርጅቱ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘውን ዋስትና ወደ ራሱ ካዝና ገቢ ያደርጋል፡፡
14. ድርጅቱ የተሸለ መንገድ ካገኘ ጨረታን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፤-093-029-3626
አልቪማ የምግብ አምራች ኃ/የተ/የግ/ማህበር