Saved to Favorites!

የፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የሰራተኛ መዝናኛ ክበብ አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ ድርጅቶች ማወዳደሪያ መስፈርቶች

Source | ምንጭ

አዲስ ዘመን ሰኔ 19/2018

Closing | መጨረሻ

Jul 06, 2026

Views | እይታዎች

40

Region | ክልል

Addis Ababa

Doc Price

200 ETB

CPO / Conditions | ሁኔታዎች

40,000

Description | ዝርዝር መግለጫ

የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር አ/ቃ/T/006/2018

በአቃቂ ቃሊቲ ከፍለ ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የሰራተኛ መዝናኛ ክበብ አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ ድርጅቶች ማወዳደሪያ መስፈርቶች
1. የህጋዊነት ጉዳዮች በተመለከተ ዕጩ ተወዳደሪዎች በዘርፉ ማለትም በሬስቱራንት ወይም በሆቴል አገልግሎት ዘርፉ የግብር ከፋይነት ምዝገባ እንዲሁም የተ.እ.ታ (ቫት) ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ የንግድ ምዝገባና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ምስከር ወረቀት ከጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ ከላይየተሰጡትን መስፈርቶች ማሟላት እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪ ካደራጃቸው የመንግስት ተቋም 6 ወር ያላለፈ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
2. የስራ ልምድ በሬስቱራንት ፣በባርና ሬስቱራንት ወይም በሆቴል አገልግሎት እንዲሁም ለጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት የስራ አገልግሎት ዘርፍ ከከ ዓመት በላይየስራ ልምድ ያለውና አሁንም በዘርፉ አገልግሎት እየሰጠ ያለ ስለመሆኑ መረጃ ማቅረብ የሚችል
3. የሰው ሀይል ድርጅቱ ቢያንስ 2000 ተጠቃሚዎችን ማስተናገድ የሚችል የሆቴል መስተንግዶ የሰው ሀይል መዋቅር አደረጃጀት ያለውና ማናጀር፣ ሼፎች/ምግብ አዘጋጆች፣ አስተናጋጆች ወዘተ መዋቅር ያለውና በድምሩ ቢያንስ 13 ሰራተኛ ያለው
4. የተሽከርካሪ ሁኔታ ድርጅቱ አገልግሎቱን በተገቢው ሁኔታ ማከናወን እንዲችል የሚያስችሉት ተሽከርካሪዎች ያለው ለምሳሌ ግብዓት ሊያቀርቡ የሚችሉ የጭነት ተሽከርካሪ ወዘተ ያለው
5. ተፈላጊ የጨረታ ማስከበሪያ CPO ብር 40,000.00 (አርባ ሺህ ብር) ሲሆን (CPO ሲያሰሩ ለአቃቂ ቃሊቲ ከፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ብለው ያሰሩ)
6. በድርጅቱ የሚሸፈኑ ግብዓቶችን በተመለከተ ድርጅቱ የውሃ፣ የመብራት እንዲሁም የቤት ኪራይ የማያስከፍል መሆኑ እና ድርጅቱ የራሱ እቃዎች ያሉት መሆኑ እና አሸናፊው አካል የራሱን ተጨማሪ እቃ በማስመዝገብ አስገብቶ መስራት የሚችል መሆኑ
7. የተጠየቀውን የጨረታ ማስከበሪያ እንዲሁም ቢያሸንፉ የውል ማስከበሪያ CPO /
የባንከ ዋስትና /በጽ/ቤታችን ስም አሰርቶ ማቅረብ የሚችል
8. ለመንግስት ንብረት ጥንቃቄ በማድረግ በሚሰራና በራሱ ወይም በሰራተኞቹ ጥንቃቄ ጉድለት ምክንያት በመገልገያ ቁሳቁስና ህንጻ ላይ ብልሽት ቢደርስ ወይም ጥፋት ቢከሰት መልሶ ለመተካት አልያም ካሳ ለመክፈል ፍቃደኛ መሆኑን ማረጋገጫ ደብዳቤ በድርጅቱ ፈርማ እና ማህተም ማረጋገጥና ማቅረብ የሚችል፡፡
9. ለካፌ ለሆቴል መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ ዝርዝር የያዘውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል መውሰድ የሚችሉ ሲሆን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በፐ/ሰ/የሰ/ሀ/ል/ፅ/ቤት የግዥ አስተዳደር ቡድን 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 508 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
10. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ መሙላት ያለባቸው ቫትን ጨምሮ ያለውን ዋጋ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ ኦርጅናል ላይኦርጅናል ኮፒ ላይ ኮፒ በማለት በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ( 10 ) ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ እየር ላይ በማዋል በአስራ አንደኛው የስራ ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት ብቻ ተጫራቾች ሰነድ በማስገባት 4፡00 ሰዓት ላይ ጨረታው ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 508 ጨረታው ይከፈታል፡፡
11.ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ የድርጅታቸውን እድራሻ ስም፣ ማህተምና ፊርማ ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡
12. ተጫራቾች ላሸነፉት ግብዓት የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 30% ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
13. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡- አድራሻ፡- ከቃሊቲ መናኽሪያ ፊት ለፊት ባለው የአስተዳደሩ
ህንፃ ላይ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 508 መጠየቅ ይቻላል፡፡
የኣቃቂ ቃሊቲ ክፍስ ከተማ ፐ/ሰ/የሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት

PDF Export is locked for your plan.